Job 20

ሶፋር

1ናዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ ሲል መለሰ፤

2“እጅግ ታውኬአለሁና፣
ሐሳቤ መልስ እንድሰጥ ይጐተጕተኛል።
3የሚያቃልለኝን ንግግር ሰምቼአለሁ፤
መልስም እሰጥ ዘንድ መንፈሴ ገፋፋኝ።

4“ሰው
ወይም አዳም ማለት ነው።
በምድር ላይ ከተቀመጠ ጊዜ ጀምሮ፣
ከጥንቱ እንዴት እንደ ነበረ ታውቃለህን?
5የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣
የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
6እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ቢልም፣
ዐናቱም ደመናትን ቢነካ፣
7እንደ ኵበት ለዘላለም ይጠፋል፤
ቀድሞ ያዩትም፣ ‘የት ገባ?’ ይላሉ።
8እንደ ሕልም በርሮ ይጠፋል፤ አይገኝምም፤
እንደ ሌሊትም ራእይ በቅጽበት ያልፋል።
9ቀድሞ ያየው ዐይን ዳግመኛ አያየውም፤
የነበረበትም ቦታ ከእንግዲህ አይመለከተውም።
10ልጆቹ ለድኾች ካሳ መክፈል አለባቸው፤
እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።
11ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣
ከእርሱ ጋር በዐፈር ውስጥ ይተኛል።

12“ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣
ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣
13አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣
በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣
14ምግቡ በሆዱ ውስጥ ይመርራል፤
በውስጡም እንደ እባብ መርዝ ይሆናል።
15የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤
እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።
16የእባብ መርዝ ይጠባል፤
የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።
17ማርና ቅቤ በሚያፈስሱ ጅረቶች፣
በወንዞችም አይደሰትም።
18የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤
ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤
19ድኾችን በመጨቈን ባዶ
አስቀርቷቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቋል።

20“ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውም
ሀብቱም ሊያድነው አይችልም።
21ያለውን አሟጥጦ ስለሚበላ፣
ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።
22በተድላ መካከል እያለ ጕስቍልና ይመጣበታል፤
በከባድ መከራም ይዋጣል።
23ሆዱን በሞላ ጊዜ፣
እግዚአብሔር የሚነድድ ቍጣውን ይሰድበታል፤
መዓቱንም ያወርድበታል።
24ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣
የናስ ቀስት ይወጋዋል።
25ቀስቱን ከጀርባው፣
የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጕበቱ ይመዝዛል፤
ፍርሀትም ይይዘዋል፤
26ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል፤
ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤
በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል።
27ሰማያት ኀጢአቱን ይገልጡበታል፤
ምድርም ትነሣበታለች፤
28በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ቤቱን ጐርፍ፣
መኖሪያውንም ወራጅ ውሃ
ወይም በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ወራጅ ውሃ ይወስድበታል ማለት ነው።
ይወስድበታል።
29እግዚአብሔር ለኀጢአተኞች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣
ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።”
Copyright information for AmhNASV